Dec 11, 2025 .
የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት (ETiCPA) ስራ የማስጀመር መርኃ ግብር ተካሄደ።


የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት (ETiCPA) ስራ የማስጀመር መርኃ ግብር ተካሄደ።
ኢንስቲትዩቱ እንደሀገር ብቁ የተመሰከረላቸው፣ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሒሳብ ባለሙያዎችን ለማፍራትና ሙያውን በኢትዮጵያ ለማሳደግ በማለም መቋቋሙ በመድረኩ ተገልጿል።
በመርኃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች፣ የአለም ባንክና የአለም አቀፉ የሒሳብ ባለሙያዎች ተወካዮች እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ መፅደቁ ይታወሳል።EBC


