Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 31, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከታይላንድ የንግድ ም/ቤት ጋር የመግባቢ ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከታይላንድ የንግድ ም/ቤት ጋር የመግባቢ ስምምነት ተፈራረመ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ እና የታይላንድ የንግድ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ቪዚት ሊምሉርቻ ሲሆኑ ስምምነቱ የተፈረመዉ በኢፌዴሪ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስና የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬዎ በተገኙበት ነዉ።
ይህ የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመዉ የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬዎ የታይላንድ አፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ኢኒሺየቲቭ ለማስጀመር በኢትዮጵያ በተገኙበት ጊዜ መሆኑ የሁለቱን አገራት የንግድና ኢንቨስተመንት ሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለዉን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነዉ።
የመግባቢያ ስምምነቱ አበይት ዓላማዎችም በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት ትብብሮች ምቹ ምህዳር መፍጠርና በአስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር፣ ለዚህም የአዲቮኬሲ ስራዎችን በጋራ ለመስራት መሆኑ በመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ላይ ሰፍሯል።
የሁለቱ አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በጋራ በሰጡት መግለጫም ኢትዮጵያና ታይላንድ ለረጅም ጊዜ የቆየ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ያላቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ አሁን በተጀመረዉ የታይላንድ አፍሪካ የኢኮኖሚ ግንኙነት ኢኒሸቲየቲቭ ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ የሁለቱን አገራት የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations has signed a Memorandum of Understanding (MoU) with the Thai Chamber of Commerce.
The MoU was signed by Dr. Kenenisa Lemmi, Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, and Dr. Visit Limlurcha, Vice Chairman of the Thai Chamber of Commerce. The signing ceremony took place at the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia in the presence of Foreign Minister Dr. Gedion Timothewos and Thailand’s Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs, Sihasak Phuangketkeow.
The signing of this Memorandum of Understanding which took place during the visit of Thailand’s Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs, Sihasak Phuangketkeow, to Ethiopia to launch the Thailand-Africa Economic Linkage Initiative demonstrates the commitment to strengthening bilateral trade and investment relations between the two nations.
The document outlines the primary objectives of the agreement: strengthening economic ties between the two countries, creating a favorable environment for trade and investment cooperation, and collaborating on key issues, including through joint advocacy efforts.
In a joint statement, the foreign ministers of the two countries noted the long-standing economic and political ties between Ethiopia and Thailand; they emphasized the need to work collaboratively to elevate this relationship to a higher level and ensure mutual benefit, leveraging the newly launched Thailand-Africa economic cooperation initiative.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia