Aug 31, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች ስብሰባውን በአዳማ አካሄደ።


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች ስብሰባውን በአዳማ አካሄደ።
በውይይት መድረኩም የምክር ቤቱ ያለፈው በጀት አመት የተግባራት አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የያዝነው የበጀት ዓመት ከፍተኛ የሥራ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን አንስተው ፤ ያለፈውን በጀት ዓመት ከተከናወኑ እጅግ ውጤታማ ስራዎች ተሞክሮዎችን በሚገባ በመቀመር ወደ ተግባራዊ የስራ ማሻሻያ መቀየር ይኖርብናል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የምክር ቤቱ ዋና ፀኃፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸው እያንዳንዱ በየደረጃው የሚገኝ ባለሙያና ኃላፊ የምክር ቤቱን ተልዕኮ እና አገራዊ ሚና በመረዳት መስራት እንዲሁም የግል ኃላፊነትን ከተቋሙ አጠቃላይ ዓላማ ጋር በማስተሳሰር የምክር ቤታችንን አቅም ወደ አዲስ ደረጃ ማሸጋገር ይጠበቅብናል ሲሉ ገልፀዋል።
በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እንዲሁም ምክር ቤቱን ለረዥም ጊዜ አገልግለው ለተሰናበቱ የእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

