Sep 05, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥና በደንበኛ አያያዝ ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥና በደንበኛ አያያዝ ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ።
ሥልጠናው የምክር ቤቱን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት፣ በደንበኞች አቀባበልና አያያዝ ላይ የተሻለ አሠራር ለመፍጠር እንዲሁም በተቋማዊ አስተዳደር ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
በሥልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የምክር ቤቱ የሰው ኃብት አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ከፍያለው እያሱ የተቋሙን የሰው ኃብት አቅም ለማሳደግ ከታችኛው የሥራ ደረጃ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የምክር ቤቱ አመራር ድረስ ወቅቱ የሚጠይቀውን ሥልጠና በመስጠት ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት በቀጣይነት ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

