ባዛሮች የምርት አቅርቦትን ተደራሽ በማድረግ፣ አምራችና ሸማችን በቀጥታ በማገናኘት ጠቃሚ ሚና አላቸው:- ሰብስብ አባፊራ


የ2019 አዲስ ዓመትን አስመልክቶ አውደ ርዕይና ባዛር መርሃ ግብር ላዘጋጁት የሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና ለሌሎች ተባባሪ አካላት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
እንዲህ ያሉ ባዛሮች የምርት አቅርቦትን ተደራሽ በማድረግ፣ አምራችና ሸማችን በቀጥታ በማገናኘት እና ፍትሃዊ የገበያ ዋጋ እንዲኖር በማገዝ ረገድ ጠቃሚ ሚና አላቸው።
በተለይም በዚህ የአዲስ ዓመት መዳረሻ ሸማቾች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እንዲያገኙ ማድረግ የንግዱ ማኅበረሰብ ኃላፊነት ነው።
የገበያ መረጋጋት የሚመጣውም በአንድ አካል ጥረት ብቻ ሳይሆን መንግሥት፣ የግሉ ዘርፍ፣ አምራቾች፣ ነጋዴዎችና የሸማቾች ትብብርና የጋራ ኃላፊነትን ይጠይቃል።
ስለሆነም የንግዱ ማኅበረሰብ ሕጋዊና ፍትሃዊ ንግድን በማጠናከር፣ ምርትን በማሳደግና የገበያ ትስስርን በመፍጠር የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትም የንግድ ትስስርን በማጠናከር እና ምቹ የንግድ ከባቢ እንዲፈጠር በመሥራት ከአባል ምክር ቤቶችና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጎን እንደሚቆም በድጋሜ አረጋግጣለሁ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
❇️❇️❇️❇️❇️
On the occasion of the 2019 Ethiopian New Year, I would like to express my appreciation to the Sheger City Chamber of Commerce and Sectoral Association and all other partners for organizing this exhibition and bazaar.
Such bazaars play an important role in making products more accessible, directly connecting producers with consumers, and helping to ensure fair market prices.
Particularly as we approach the New Year, it is the responsibility of the business community to ensure that consumers can access products at reasonable and affordable prices.
Market stability cannot be achieved through the efforts of one part alone. It requires cooperation and shared responsibility among the government, the private sector, producers, traders, and consumers.
Therefore, I take this opportunity to call upon the business community to play its part by strengthening legal and fair trade practices, increasing production, and creating stronger market linkages.
I would also like to reaffirm that the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) stands alongside its member chambers and various stakeholders in strengthening business linkages and working to create a conducive business environment.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

