Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 05, 2026 .

ከ2019 አዲስ ዓመት መድረስ ጋር ተያይዞ፣ የሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው የአዲስ ዓመት አውደ ርዕይና ባዛር በሞቅ ድምቀት በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል።

ከ2019 አዲስ ዓመት መድረስ ጋር ተያይዞ፣ የሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው የአዲስ ዓመት አውደ ርዕይና ባዛር በሞቅ ድምቀት በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል።

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በምክትል ፕሬዚደንት ማእርግ የሸገር ከተማ ከንቲባ ታሾመ አዱኛ(ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፤ በምርት አቅርቦት እና ጥራት ላይ ብቻ ሳይሆን ጠንካራ የገበያ ትስስር መፍጠር ላይ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተጨማሪም የገበያ ሁኔታው ምቹ እየሆኑ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ ተመሳሳይ የዋጋ ማረጋጊያ ባዛሮች ትኩረት እንደሚሰጣቸው አስታውቀዋል።

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ገሾ በበኩላቸው በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ የባዛር መርሃ ግብሮች እንደተዘጋጁ ገልጸው፣ ገበያን በማረጋጋት ረገድ ባዛሮቹ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።

የሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ሙሉጌታ ሙሊሳ፣ ባዛሩ በሸገር ከተማ የተዘጋጀው የገበያ ዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ፣ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር እንዲሁም የከተማዋን የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎች ለማስተዋወቅ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ ኩማላ ህርፋ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት በማስተላለፍ፣ መርሃ ግብሩን ላዘጋጁ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም የሻገር ከተማ የንግድ ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ ባሪሶ ተማስጌንና በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ ኃላፊዎች በመርሃ ግብሩ ተገኝተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia