Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 10, 2026 .

  

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በBRICS የቢዝነስ ፎረም ላይ ፤ በኢትዮጵያ የአቪዬሽንና የአግሪቢዝነስ ዘርፎች ስላሉ ተጨባጭ እድሎች ዙሪያ ገለፃ አቀረቡ።

ዋና ጸሐፊው ከምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል መጋቢ ታዬ ለታ ጋር በመሆን በአቪዬሽንና አግሪቢዝነስ ዙሪያ እየተካሄደ ባለ ውይይት ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ነው።

በውይይቱም የኢትዮጵያን ልምድ፣ ቀጣይ ተግባራትና ከBRICS+ አባል አገራት ጋር ሊኖሩ የሚችሉ የትብብር እድሎችን የተመለከተ ገለጻ ቀርቧል።

በአቪዬሽን የስራ ቡድን ውይይት ዶ/ር ቀነኒሳ ኢትዮጵያን አፍሪካን ከዓለም ጋር ለማገናኘት ያላትን ስትራቴጂካዊ ሚና እና በዘመናዊ የአቪዬሽን መሠረተ ልማት ላይ የምታደርገውን ኢንቨስትመንት በስፋት ዳስሰዋል። ከ110 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን በዓመት ለማስተናገድ አቅም የሚኖረው አዲሱ ሜጋ ኤርፖርትም የኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ማዕከልነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

በተጨማሪም ፤ የኢትዮጵያ የአቪዬሽን አካዳሚ ያለውን የላቀ ልምድ እና በሰው ሰራሽ እውቀት (AI) እና በቴክኖሎጂ ትምህርት የሚፈጠሩ አዳዲስ እድሎች በBRICS+ ማኅበረሰብ ውስጥ ለሰው ኃይልና ለክህሎት ልማት ጠቃሚ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚችሉም አመልክተዋል።

በአግሪቢዝነስ የስራ ቡድን ውይይም ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ማስፋፋት ያስመዘገበችውን ልምድ እና የምግብ ዋስትናንና የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻል የምታደርገውን ጥረት አብራርተዋል።

በማብራሪያቸውም የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ለአየር ንብረት ፣ ለአካባቢ ልማት ዘላቂነት እና የግብርና ልማት ጠቃሚ መድረክ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

BRICS+ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማስፋፋት፣ እውቀትና ቴክኖሎጂን ለመለዋወጥ፣ የሰው ኃይልን ለማልማት እንዲሁም በአባል አገራት መካከል ለንግዶችና ለአነስተኛ፣ ለጥቃቅንና መካከለኛ (MSMEs) ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር ጠቃሚ መድረክ መሆኑንም ገልጸዋል።

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations
Secretary General Dr. Kenenisa Lemi has highlighted Ethiopia’s aviation and agribusiness opportunities at the BRICS Business Forum.

The Secretary General attended the Aviation and Agribusiness Working Group sessions alongside ECCSA Board of Directors member Megabi Taye Leta, where he presented Ethiopia’s experience, ongoing initiatives and emerging opportunities for cooperation with BRICS+ economies.

In the aviation session, the Secretary General highlighted Ethiopia’s efforts to strengthen its position as a gateway between Africa and the rest of the world, including investment in modern aviation infrastructure. He also outlined plans for a new mega airport designed to handle more than 110 million passengers annually.

He further noted Ethiopia’s established aviation academy and emerging opportunities in artificial intelligence and technology education as potential areas for skills and human capital development.

During the agribusiness session, he highlighted Ethiopia’s progress in expanding wheat production and strengthening food security and agricultural productivity. He also underscored the Green Legacy Initiative as an important platform for climate resilience, environmental sustainability and long-term agricultural development.

He further said BRICS+ offers opportunities to expand trade and investment, share knowledge and technology, develop human capital and create new opportunities for businesses and MSMEs across member economies.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia