Jun 25, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድ ልዑካን ቡድን በጃፓን ኦሳካ ከተማ ከጃፓን ኩባንያዎች ጋር የአቻ ለአቻ ውይይት አካሄደ::



የኢትዮጵያ የንግድ ልዑካን ቡድን በጃፓን ኦሳካ ከተማ ከጃፓን ኩባንያዎች ጋር የአቻ ለአቻ ውይይት አካሄደ::
(ኦሳካ ጃፓን – ጁን 26, 2025 ) በኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ምህበራት ምክር ቤት እና በጃፓን የኢትዮጵያ ኤንባሲ በጋራ ትብብር እንዲሁም በኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናው ትስስር ሚኒስቴር ፤ በኢንደስትሪ ፓርኮችና በዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጠንካራ ተሳትፎ እየተካሄደ ያለው የጃፓን – ኦሳካ የንግድ ትርኢት አካል የሆነው የአቻ ለአቻ ዉይይት ዛሬ ተካሂዷል:
በውይይቱም፣ ተወካዮቹ በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎች እንዲሁም በኢንዱስትሪ ልማት ዙርያ ሰፊ ዉይይት ያደረጉ ሲሆን በጋራ ሊተገበሩ በሚችሉ ስራዋች ዙሪያ መግባባት ላይ ተደርሷል ::
በውይይቱም በጃፓን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ፤ የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ምህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢርን ጨምሮ
ሌሎች ኃላፊዎችና ከሁለቱም አገራት የተወጣጡ የንግዱ ማኀበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።




