Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 23, 2025 .

በመዲናዋ ከ3 ሺህ በላይ ባለሐብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል::

በመዲናዋ ከ3 ሺህ በላይ ባለሐብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል::

▶️ በአዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ባለሐብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አይሻ መሀመድ እንደገለጹት፤ በ2017 በጀት ዓመት 8 .5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከ3 ሺህ 200 በላይ ባለሐብቶች ፍቃድ ወስደው ወደስራ ገብተዋል፡፡

▶️ ኮሚሽኑ ለባለሐብቶቹ የተለያዩ ማበረታቻዎችን እያቀረበ እንደሚገኝም ጠቁመው፤ ከማበረታዎቹ መካከል እንደ ዘርፎቹ የገቢ ግብር እፎይታ ከ3 እስከ 5 ዓመት እንዲሁም የማምረቻ ቦታ እና ማሽነሪ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም ከ3 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ኢንቬስተሮች ፈቃድ ይሰጣል እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

▶️ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል እንዲያስመዘገቡ እንዲሁም ከ7 ሺህ 500 በላይ ለሚሆነ ዜጎችም የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውቀዋል።

▶️ በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማዘመን የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ፣ አዲስ አበባ ያላትን እምቅ ሀብት ማስተዋወቅ፣ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ማሳለጥ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በቅንጅት የመፍታት ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

▶️ ኢንቨስትመንቱን ለማሳደግ የመሶብ የአንድ ማዕከል  አገልግሎት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሯ፤ ባለፈው በጀት ዓመት የማምረቻው ዘርፍ አፈፃፀም ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰዋል።
ምንጭ – EBC

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia