Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 12, 2025 .

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን  በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ስምምነት መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ  የስሪት አገር ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሰጥቷል።

በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ስምምነት መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ  የስሪት አገር ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (Certificate of origin)
እነማን ወሰዱ?

▶️ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን  በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ስምምነት መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ  የስሪት አገር ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሰጥቷል።

ሰርተፊኬቱ ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ እና ኬኒያ የኢትዮጵያ  ምርት የሆኑ እቃዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት መሰረት ለሚልኩ ሁለት ድርጅቶች የተሰጠ ነው።

▶️ የጉምሩክ ኮሚሽን ለእቃዎች ንግድ ታሪፍ ቅነሳ  ወሳኝ መሳሪያ የሆነውን የስሪት ሀገር የምስክር ወረቀት (Certificate of origin) በአህጉራዊ ነጻ ንግድ ስምምነት ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጥንቃቄ መስፈርት (Security Features መሠረት ለህትመት የማብቃት እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ኮሚሽነሩ ደበሌ ቃበታ ገልፀዋል፡፡

▶️ የመጀመሪውን እና ሁለተኛውን የስሪት ሀገር ማረጋገጫ ሰርትፊትፍኬት Lampros Trading PLC  በድምሩ 96 ሜትሪክ ቶን ነጭና ቀይ  ቦሎቄ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ እና

▶️ ሶስተኛውን የስሪት የስሪት ሀገር ማረጋገጫ ሰርተፍኬት Belayeneh Kinde Mekonnen 400.8 ሜትሪክ ቶን በቆሎ ወደ ኬንያ ኤክስፖርት በማድረግ በይፋ ኢትዮጵያ ንግዱን ባለፈው ሐሙስ ጀምራለች፡፡

▶️ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ስምምነት  ኢትዮጵያን ጨምሮ በ54 የአፍሪካ ህብረት አገራት  ተፈርሞ እ.ኤ.አ  ከግንቦት 30  ቀን 2019 ጀምሮ ጽ/ቤቱን (AfCFTA Secretariat) በጋና አክራ ከፍቶ ወደ ትግበራ ሂደት የገባ በአባላት ብዛት ትልቁ ነፃ የንግድ ቀጠና ሲሆን የሀገራችንም የእቃዎች ንግድ ታሪፍ ኦፈር በሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 574/2017 በይፋ መታወጁ የሚታወስ ነው።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia