Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 24, 2025 .

ባለፉት ሶስት ወራት የተሰበሰበው የፌደራል መንግስት ገቢ 323 ቢሊየን ብር ደርሷል::

ቁጥሮች ምን ይነግሩናል ?

❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️

▶️ ይህ አፈጻጸም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ112 በመቶ ጭማሪ ያለው ሲሆን ÷ በወቅቱ የተሰበሰበው ገቢ 152 ቢሊየን ብር ነበር፡፡

▶️ ባለፉት ሶስት ወራት ከወርቅ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር  ገቢ ተገኝቷል፤

▶️ ከቡና ደግሞ 763 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል

▶️ ባለፉት 100 ቀናት ከአጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ 8.29 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ፤

▶️ ከወጪ ንግድ የሚመጣው የውጭ ምንዛሪ 57.6 በመቶ ደርሷል።

▶️ ባንኮች ባለፉት ሦስት ወራት እርስ በርሳቸው 19.2 ሚሊዮን ዶላር ሲያገበያይ፤ ብሔራዊ ባንክ ደግሞ 150 ሚሊዮን ዶላር አጫርቷል።

▶️ የሃዋላ ፍሰት 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፤

▶️ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ደግሞ 961 ሚሊየን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

▶️ አጠቃላይ ተቀማጭ ሃብት 3 ነጥብ 73 ትሪሊየን ብር ደርሷል ፤

▶️  በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የሥራ ስምሪት ለ671 ሺህ 589 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡

▶️ በዚህ መሰረትም በሀገር ውስጥ ለ535 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን፤

▶️ ከዘርፍ አንጻርም

❇️ በግብርና ለ186 ሺህ ፣
❇️ በኢንዱስትሪ ለ122 ሺህ እንዲሁም
❇️ በአገልግሎት ለ227 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።

▶️ በተመሳሳይ በውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ለ136 ሺህ 589 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤

▶️ በተኪ ምርትም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል

▶️ ባለፉት ሦስት ወራት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በ13 በመቶ በማደግ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገቱን እየመራ ነው፤

▶️ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት በጠቅላላ 132 አዳዲስ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ገብተዋል።

▶️ ለግሉ ዘርፍ እና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች የሚደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ከፍ ማለቱ በዘርፉ ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ተመላክቷል።

▶️ በሌላ በኩል ባለፉት ሶስት ወራት በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ ሥራ መከናወኑ ተሰርቷል፤

▶️ በዘርፉ በአጠቃላይ 242 ሚሊየን ኩንታል ምርት የተሰበሰበ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 74 ነጥብ 73 በመቶው የሰብል ምርት ነው ፤

▶️ 2.45 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ የሆርቲካልቸር ምርቶች እየለሙ ነው።

▶️ የሆርቲካልቸር ዘርፉ ልማት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር የ31.7 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፤

▶️ ባለፉት መቶ ቀናት 376 ሺህ 615 የውጭ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፤

▶️ 29 ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ማዘጋጀት ተችሏል፤

▶️ በእነዚህ ኮንፈረንሶች ላይም 35 ሺህ 115 የውጭ ሀገር ዜጎች ተሳትፈዋል፤

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia