Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 28, 2025 .

ባለፈው አመት ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢኮኖሚን በተመለከ ያንሷቸው  ነጥቦች….

▶️ ባለፈው አመት ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።

▶️ የቡና ምርትን ከነበረበት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ባለፈው ዓመት 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ ተችሏል፤

▶️ ቡና በሀገር ውስጥ ያለውን ፍላጎት ሸፍኖ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ንግድ ተገኝቷል፤

▶️  ሩዝን ከነበረበት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63  ሚሊዮን ኩንታል ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የስንዴ ምርትንም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 280 ሚሊዮን ኩንታል በአጠረ ጊዜ ውስጥ አሳድግነዋል።

▶️ ያለፈው በጀት ዓመት  ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል።

▶️ ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም በቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል። በዚህም የኢትዮጵያ ሪዘርቭ በ10 እጥፍ አድጓል።

▶️የዚህ አመት የጥቅምት ወር የዋጋ ንረት 11 ነጥብ 7  በመቶ ወርዷል።

▶️  ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2032 በአፍሪካ 2ኛ በ2036 ደግሞ ከአፍሪካ የመጀመሪያውን ኢኮኖሚ ይኖራታል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia