Oct 30, 2025 .
የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዴሌይቲ(Deloitte) ከተሰኘዉ የጃፓን የቢዝነስ አማካሪ ድርጅት ጋር ተወያይቷል።

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዴሌይቲ(Deloitte) ከተሰኘዉ የጃፓን የቢዝነስ አማካሪ ድርጅት ጋር በሶላር ኢነርጂ ላይ ከሚሰራዉ TERRA ከሚባል ድርጅት ጋር የኢትዮጵያ ቢዝነሶች በአጋር ሊሰሩ በሚችሉባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ተወያይቷል።
የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የኢትዮጵያ መንግስት ለዉጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ካደረጋቸዉ የቢዝነስ ዘርፎች ታዳሽ ኢነርጂ አንዱ መሆኑን ጠቅሶ በሶላር ኢነርጂ ላይ ከሚሰራዉ TERRA የተሰኘ ድርጅት ጋር በዘርፉ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ቢዝነሶችን ማስተሳሰር ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ስኬት አስተዋፅኦ ማድረግ ነዉ ብለዋል።

በDeloitte አማካሪ ድርጅት የመንግስትና ፐብሊክ ሰርቪስ ከፍተኛ አማካሪ ሂሮኮ ሆዋኪ እና የመሰረተ ልማትና ካፒታል ፕሮጀክቶች ከፍተኛ አማካሪ ኬንታ ሚያሞቶ በበኩላቸዉ የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ ለስደተኞችና አገር ዉስጥ ተፈናቃዮች የስራ ዕድል መፍጠርና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ መሆኑን አስረድተዉ ይህንን ለማሳካት TERRA ከኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳለዉ አረጋግጠዋል።

