Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 07, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ የአርባ ምንጭ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ የአርባ ምንጭ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የንግድ ምክር ቤቱ የቦርድ አባላት ከፕሬዚዳንቱ ጋር በነበራቸው ውይይት ወደ ፊት ሊሰሩ በሚገባቸው የትብብር ስራዎች እንዲሁም መተግበር ባለባቸው የተሻሉ አሰራሮች ዙሪያ ተነጋግረዋል፡፡

አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ምክር ቤቶች ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እንዲሁም የክልል እና የከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች እርስ በርስ ያሏቸውን መልካም ተሞክሮዎች በመለዋወጥና በመተባበር ተሰሚነታቸው ከፍ እንዲል መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸውም የንግዱ ማኅበረሰብ የሚያጋጥሙትን የተለያዩ ችግሮች ከሚመለከታቸው የመንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር መፍታት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቦጋለ ቢታኔ በበኩላቸው ምክር ቤቱ ላደረገላቸው ትብብር ያላቸውን ምስጋና ገልጸው ለወደፊትም የምክር ቤቱ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል መጋቢ ስርዓት ቀሲስ ታዬ ለታ እንዲሁም የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ተገኝተዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላትም ለኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ኃላፊዎች የክብር ስጦታ አበርክተዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia