Nov 07, 2025 .
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 1ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ የቦርድ ስብሰባውን በቡታጅራ ከተማ አካሄደ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 1ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ የቦርድ ስብሰባውን በቡታጅራ ከተማ አካሄደ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 1ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ የቦርድ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በቡታጅራ ከተማ አካሄዷል።
የቦርድ ስብሰባው የክልሉ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሳኒ ሀሰን እና ም/ፕሬዝዳንት አቶ ወንደሰን አርጋው እንዲሁም የቦርድ አባላቱ በተገኙበት ተካሃዷል።
የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤቱ ስብሰባ የ2017 ዓ/ም አመታዊ የስራ ሪፖርት እና የ2018 ዕቅድ በማዳመጥ በመገምገም እና በማፅደቅ እንዲሁም በተለያዩ የምክር ቤቱ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ተጠናቋል። (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት)

