የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት ያለፉት አራት ወራት አፈጻጸም የንግድ ዘርፍ የሴክተር ጉባኤ ቢሾፍቱ በማካሄድ ላይ እንገኛለን:-ዶክተር ካሳሁን ጎፌ

በዛሬው ዕለት የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት ያለፉት አራት ወራት አፈጻጸም የንግድ ዘርፍ የሴክተር ጉባኤ የቱሪዝም መዳረሻ በሆነችው በውቢቷ ቢሾፍቱ በማካሄድ ላይ እንገኛለን።
በሀገር ውስጥ ንግድ የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥን ሽፋን ከማሳደግ አንጻር በበጀት ዓመቱ ባለፉት አራት ወራት 968,333 ለመፈጸም ታቅዶ 1,382,598 ማከናወን ተችሏል።
ይህም የዕቅዱ 142% አፈፃጸም ሆኖ ተመዝግቧል።
በወጪ ንግድ ግኝት አፈፃፀም ረገድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት 3.37 ቢሊዮን ዶላር ወይም 119 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡
ይህ የወጪ ንግድ አፈፃፀም ከባለፋ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር የ1.53 ቢሊዮን ዶላር ወይም 83.7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር በገቢ ዕቃዎች፣ የወጪና ሌሎች ምርቶች ላይ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል። የዲጂታል ንግድን ከማስፋፋትና የግብይት ስርዓትን ከመዘርጋት አንፃር ባለፉት አራት ወራት የኢ-ኮሜርስ የግብይት ፕላት ፎርም ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን መረጃ የማሰባሰብና የማደራጀት ስራ ተከናውኗል።
በተጨማሪም በኢ-ኮሜርስ ንግድ ትግበራ ላይ የታዩ ተግዳሮቶችን በመለየት የኢ-ኮሜርስ የሙከራ ሳጥን የማዘጋጀት ስራ ተከውኗል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት በላክናቸው ምርቶች በደመቀ መረሃ ግብር አስጀምረናል።
በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት 6ኛውን የስራ ቡድን ስብሰባ አባል ሃገራቱ በኢትዮጵያ ቁርጠኝነትና የመከወን አቅም እንዲተማመኑ ያስቻለ ውጤት ተመዝግቦበታል።
ዶክተር ካሳሁን ጎፌ
የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

