Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 13, 2025 .

በፍጥነት እያደገ ላለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቀጣይነት ጠንካራ ተቋማት፣ አስተማማኝ የፋይናንስ ሥርዓት እና ብቁ የሰው ሃይል መኖር ወሳኝ መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።

 

▶️ በፍጥነት እያደገ ላለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቀጣይነት ጠንካራ ተቋማት፣ አስተማማኝ የፋይናንስ ሥርዓት እና ብቁ የሰው ሃይል መኖር ወሳኝ መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።

▶️ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ለተመሰከረላቸው የኢትዮጵያ ሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ስያሜ ይፋ የማድረግ እና የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

▶️ በመድረኩ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እንዳሉት የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫ ጠንካራ ተቋማትን አስተማማኝ የፋይናንስ ስርዓት እና ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያስቀጥል የሰለጠነ የሰው ኃይል ይጠይቃል።

▶️ የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ወደ ስራ መግባት የፋይናንስ ዘርፉን ትራንስፎርሜሽን ለማሳለጥ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።

▶️ በተጨማሪም ለፋይናንስ ስርዓቱ የጀርባ አጥንት ከመሆን ባለፈ አስተማማኝ የፋይናንስ ዘርፍ እንዲፈጠር፣ ህብረተሰቡ ስለፋይናንስ ዘርፉ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው እና ለውሳኔ ሰጪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት።

▶️ ይህም የኢኮኖሚ ዕድገትና ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።

▶️ ካሁን ቀደም የሂሳብ ባለሙያዎች ማረጋገጫ የሚቀበሉት ከውጭ ተቋማት መሆኑን አስታውሰው፥ ኢንስቲትዩቱ ይህንን ተግባር በሀገር ውስጥ ማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል።

▶️ ኢንስቲትዩቱ በተቋማት አሠራር ግልፅነት እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ የሂሳብ አያያዝ፣ ኦዲት እና የፋይናንሺያል ሪፖርት መረጃዎችን የማስተዋወቅ እና የማሳደግ አላማ እንዳለውም ጠቅሰዋል።

▶️ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ዘመናዊ፣ ግልጽ የሆነና ለችግር የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት የራሱ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

▶️ ኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ የዘርፉ ተቋማት ፈቃድ ባላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች የታገዘና ደረጃውን የጠበቀ የሂሳብ ሪፖርት እንዲያዘጋጁ ያስችላቸዋል።

▶️ ይህም የሂሳብ ሪፖርቶች ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያሟሉ በማድረግ የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

▶️ ኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ አጎናፍር በኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ቢኖሩም የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር በጣም አነስተኛ ነው ብለዋል።

▶️ ኢንስቲትዩቱ ወደ ሥራ መግባቱ በዘርፉ ብቃት ያለው ከፍተኛ የሰው ሃይል ማፍራት እንደሚያስችልም አንስተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia