Dec 24, 2025 .
የማዕድን ሚኒስቴር በከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረትና የነዳጅ ስራዎች የጋራ ገቢ (ሮያሊቲ) አሰባሰብና ክፍፍል አፈጻጸም ላይ ከክልሎች ጋር የውይይት መደረክ አካሂዷል።


የማዕድን ሚኒስቴር በከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረትና የነዳጅ ስራዎች የጋራ ገቢ (ሮያሊቲ) አሰባሰብና ክፍፍል አፈጻጸም ላይ ከክልሎች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የውይይት መደረክ አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የክልል የማዕድን፣ የገቢዎች እና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በመደረኩ ከዚህ በፊት የነበሩ አፈጻጸሞች ተገምግመው ወደፊት በጋራ ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮች ላይም አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

የማዕድን ሚኒስቴር በማዕድን ስራዎች አዋጅና ደንብ መሰረት ከከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረት ባለፈቃድ ኩባንያዎች የሚሰበሰበውን የጋራ ገቢ (ሮያሊቲ) ይሰበስባል።
ከአምራች ኩባንያዎች የተሰበሰበው ሮያሊቲ ገቢ በተፈቀደው የጋራ ገቢ ማከፋፈያ ቀመር መሰረት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ይከፋፈላል።
መደረኩ በፌዴራልና በክልል መንግስታት መካከል ትብብርን ለማጠናከር፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማሻሻል እንዲሁም የጋራ ገቢ አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል::

