Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jan 28, 2026 .

የግሉ ዘርፍ በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ዉስጥ ሚናዉን እንዲጫወት ም/ቤቶችን መደገፍና ማጠናከር የግድ መሆኑን የሲዳማ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩርያ አስታዉቀዋል።

  

የግሉ ዘርፍ በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ዉስጥ ሚናዉን እንዲጫወት ከተፈለገ ንግድ ም/ቤቶችን መደገፍና ማጠናከር የግድ መሆኑን የሲዳማ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩርያ አስታዉቀዋል።

ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና ከክልሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዲይሬክተሮች ቦርድ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደ ክልል የንግድ ም/ቤት ከእኛ ጋር ተቀራርቦ እየሰራ ነዉ፣ የግሉ ዘርፍና መንግስት ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረዉ አገናኝ የሆነዉ የንግድ ም/ቤት መጠናከር እንዳለበት የክልሉም መንግስት አምኖበት አሰፈላጊዉ ድጋፍ የፖለቲካ ተጠሪዉ በሆነ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ  እንዲሰጥ አቅጣጫ ተሰጥቶታል ብለዋል።

አገር አቀፉ  የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤትም በክልል ደረጃ ያሉትን ም/ቤቶች  ለማጠናከር ወርዶ መደገፍ፣መከታተልና ሁሉም ክልሎች ዉክልና እንዲኖራቸዉ የሚያስችል አሰራር መፍጠር አለበት ብለዋል ወ/ሮ ሰላማዊት።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia