Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com
Latest News
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባል ምክር ቤቶችን ተቋማዊ አቅም እንዲሁም የአሠራር ብቃትን ለማጠናከር የጀመረውን የአቅም ግንባታ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እያከናወነ ነው። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በተካሄደው 8ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ ተገለጸ። በንግድ ዘላቂነት እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት ስትራቴጂካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቋል። የካፒታል ጋዜጣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ሰፊ፣ዝርዝርና ሙያዊ ቆይታ አድርጓል። በተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራውና የምክር ቤቱን የቦርድ አባላት ያካተተው ልዑክ፣ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በኤግዚቢሽኑ ተሳትፏል። ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ማኅበረሰብ ጋር ማገናኘት የውጭ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉብኝቶቻችን ዋነኛ ዓላማ ነው።

Read more

Feb 04, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር  ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከጥር 27 -የካቲት 01 ቀን  2018 ዓ.ም የሚካሄደው 15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት ተከፈተ፡፡   

የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር  ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከጥር 27 -የካቲት 01 ቀን  2018 ዓ.ም የሚካሄደው 15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት ተከፈተ፡፡

በመክፈቻ ስነስርዓቱም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶክተር) እና ሚኒስተር ደኤታዎች፣  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር እና መላው የዴሬክተሮች ቦርድ አባላት እንዲሁም  የምክር ቤቱ ዋና ጸኃፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ተገኝተዋል።

የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በተገኙበት የተከፈተውና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ የንግድ ትርሂት የኢትዮጵያን ምርቶች፣ አገልግሎቶችና ግብዓቶች በማስተዋወቅ፣ ለአገራችን ኢንዱስትሪ ልማት እድገት፣ ለስራ ፈጠራ እና ለንግድ ስራ መስፋፋት የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች የሚቀርቡበት ነው፡፡

በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው የንግድ ትርኢት ላይ ከ20 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እንዲሁም ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን በማቅረብ ይሳተፋሉ።

የንግድ ትርኢቱ በመስቀል አደባባይ  ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከዓለም ዓቀፍ የንግድ ተቋማት እና በአገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞች  ምርቶች እና አገልግሎቶች ይቀርባሉ እንዲሁም የአቻ ለአቻ የንግድ መድረክም ይካሄድበታል ፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia