Mar 20, 2026 .
ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ-ኮሜርስ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ-ኮሜርስ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
የሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ብሥራት በለጠ ወጣቶች በሥራ ላይ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮች ለመፍታት በየጊዜው በሚሰጡ ስልጠናዎች ራስን ማብቃት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ስልጠናው ለወጣቶች ዘመናዊ አሰራርና ግብይትን እንዲያውቁ እንዲሁም ምርትና አገልግሎታቸውን በቀላሉ ለደንበኞቻቸው ማድረስ እንደፊችሉ ያግዛል ተብሏል፡፡



ምርትና አገልግሎቶች ለአካባቢያዊ፣ ለቀጣናዊና አለም አቀፍ ገበያ በቀላሉ ለመድረስ አጋዥ እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡
ሰልጣኞችም ያገኙት ስልጠና ዘሙን የሚመጥንና በስራቸው ላይ ለውጥ ለማምጣት አጋዥ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡ ለሰልጣኞቹም ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በቢዝነስ አመራር አካዳሚው በኩል በተለያዩ የስልጠና መስኮች ፍላጎትን መሰረት በማድረግ በተለይም ለሴቶች፣ ለወጣቶችና ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

