Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Mar 28, 2026 .

ንግድ ሳይንስ በሆነበት ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት በእውቀት  መምራት ያስፈልጋል:- ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ

ንግድ ሳይንስ በሆነበት ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት የንግድ ክህሎትን ማሳደግና  በእውቀት  መምራት ያስፈልጋል ሲሉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ  ማኅበራት ምክር ቤት  ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ገለፁ ።

ይህንን የተናገሩት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለንግድ ምክር ቤቶች ዋና ፀሐፊዎች  በ”Chambers leadership and Governance “በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል የአቅም  መጎልበቻ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ነው ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተልዕኮዎቹ አንዱ የአባላትን አቅም መገንባት መሆኑን ገልጸው ዋና ፀሐፊዎችም “የሊደርሽፕና ገቨርናንስ”  እውቀትና  ክህሎታቸውን በማሳደግ የመሪነት ሚናቸውን መወጣት እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጣና መቀላቀሏን እንዲሁም  የአለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል በሂደት ላይ መሆኗ  ለንግዱ ማህበረሰብ  መልካም አጋጣሚ ነዉ: ይሁን እንጂ   መጪው ጊዜ ውድድር  የሚጠይቅ በመሆኑ  መዘጋጀትን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የንግድ ምክር ቤቶች ኃላፊዎችም ንግድ እንዲዘምን ፣ ሳይንሳዊ እንዲሆን መስራት እንዳለባቸው አሳሰበው አጠቃላይ የንግድ   ኮሙኒኬሽን ስርዓቱን  የሚፈትሹና የሚያዘምኑ ፣   ራሳቸውን የሚያበቁ መሆን እንዳለባቸው  ገልፀዋል ።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia