Apr 14, 2026 .
የኢትዮ ቤላሩስ የቢዝነስ ፎረም

ለንግዱ ማህበረሰብ
የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ የኦሮሚያ ንግድ ምክር ቤት እና የቤላሩስ ንግድ ምክር ቤት በጋራ በመተባበር ኤፕሪል 16 ቀን 2026 ከጧቱ 3፡00 ጀምሮ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ከቤላሩስ ሀገር የሚመጡ ግዙፍ ኩባኒያዎች ከፍተኛ ሃላፊዎች ባሉበት የኢትዮ ቤላሩስ የቢዝነስ ፎረም አዘጋጅተናል፡፡ በመሆኑም በቢዝነስ ፎረሙ ላይ በመሳተፍ ያልተነካዉን የቤላሩስ ገበያ በመቀላቀል እድሉን ለመጠቀም ፍላጎት ያላችሁ የሀገራችን አምራቾች፣ አስመጪና ላኪዎች ቀድማችሁ እስከ ኤፕሪል 14 ብቻ በሊንክ https://forms.gle/1mWj2LrsJj7uTkVf9 በመመዝገብ እንዲትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
ማሳሰቢያ
• ያለዉ ቦታ የ20 ሰዉ ብቻ ነዉ፡፡
• የሚመጡት የቤላሩስ ኩባኒያ ፕሮፋይል ዋትሳፕ ግሩፑ ላይ ከታች ተያይዟል፡፡
• ለበለጠ መረጃ በ0917809005 መደወል ይቻላል

