ምክር ቤታችንን ከየአገራቱ ፍላጎቶች አንፃር በበቂ እና ወቅታዊ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮችን በሚያሳይ እና በሚተነትን ሙሉ መረጃ የምናጠናክር ይሆናል:- ሰብስብ አባፊራ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የስራ ኃላፊዎች ከቻይና የዥጂያንግ የንግድና ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ልዑካን በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮችና ምቹ እድሎች ዙሪያ ተወያይተዋል ።
ኩባንያዎቹ በሪል እስቴት ግንባታ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኃይል አቅርቦት እና በሌሎችም ዘርፎች በኢትዮጵያ የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው የገለፁ ከመሆኑ አንፃር በአገራችን ስላለው ሰፊ አማራጭ፣ የገበያ እድል፣ አስቻይ የመንግስት ፖሊሲዎችና በመንግስት እየተከናወኑ ስላሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎች፣ የአፍሪካ ነፃ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና(AfCFTA) ስለሚያስገኛቸው የገበያ እድሎች እንዲሁም በዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅት(WTO) አባልነት ሁኔታ ስለምንገኝበት ሁኔታ ማብራሪያ ቀርቧል።
የቻይና የዥጂያንግ የንግድና ኢንዱስትሪ ፌደሬሽንን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የሚመጡ የንግዱ ማኀበረሰብ አካላት ከምክር ቤታችን ጋር ለመስራት እንዲሁም በአገራችን ስላለው የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች የበለጠ ለመረዳት በስፋት የሚመርጡን በመሆኑ ፤ ምክር ቤታችንን ከየአገራቱ ፍላጎቶች አንፃር በበቂ እና ወቅታዊ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮችን በሚያሳይ እና በሚተነትን ሙሉ መረጃ የምናጠናክር ይሆናል።
እንዲሁም ፤ አገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በዘርፋ ስላላቸው ፋይዳ፣ በየኢንቨስትመንት ዘርፋ ስለሚኖሩ ማበረታቻዎችና ሕጎች እንዲሁም ሌሎች አገራዊ ፣ አካባቢያዊ ፣ አህጉራዊና ዓለምአቀፍ ተያያዥ ሁኔታዎችን በመተንተንና ለየመረጃ ፈላጊዎቻችን በቂ እና አጥጋቢ ምንጭ መሆን ይገባናል።
በተጨማሪም ከተለያዩ አገራት የሚመጡ ኢንቬስተሮች ፍላጎቶችን በበቂ ሁኔታ በማጠናቀር ከሚመለከታቸው የየዘርፋ ሚኒስቴር መ/ቤቶች እንዲሁም ኮሚሽን እና ሌሎች ተቋማት ጋር እንዲገናኙና ተጨማሪ ግብዓት እንዲያገኙ ማመቻቸት የምናከናውነው ተግባር ይሆናል።
ከዚህም ባሻገር፤ ከምክር ቤታችን አንፃር በቂ የኢንቨስትመንት ውጤታማነት ክትትል ማድረግ የሚያስችለንን አሰራር በማስቀመጥ ምን ያህሉ ኢንቬስትመንቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ውጤታማ እንደሆኑ ወይም ስኬታማ ያልሆኑትን ከነየምክንያቶቹ በመተንተን ከመንግስት አስፈጻሚ አካላት ጋር በሚኖሩን የጋራ መድረኮች(EPPDF) መነሻ የውይይት ጭብጦች ሊሆኑን ይገባል።
በመሆኑም የንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ስራዎች ዓለም አቀፍ አሰራር በመሆኑ ወይም በማቋቋሚያ አዋጃችን የተሰጠን አንዱ ተግባራችን ስለሆነ ብቻ የምንከውነው ሳይሆን፤ ለአገር ውስጡ የግሉ ዘርፍ የአሰራሮች፣ የልምድና የተሞክሮ መቅሰሚያ በመሆኑ እንዲሁም ለስራ ዕድል ፈጠራ፣ ለውጪ ምንዛሬ ግኝት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ወሳኝ ሚና ስለሚኖረውም ጭምር ነው።
በመሆኑም ሁላችንም በዚህ የአሰራር ማዕቀፍ ውስጥ ልንንቀሳቀስ ይገባል መልዕክቴ ነው::
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
The management of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) held discussions with a delegation from the Zhejiang Federation of Industry and Commerce of China on Ethiopia’s trade and investment opportunities and favorable business environment.
Given that the visiting companies expressed interest in investing and operating in Ethiopia in sectors such as real estate development, manufacturing, energy supply, and other areas, presentations were made on the country’s vast investment potential, market opportunities, supportive government policies, ongoing economic reform measures, opportunities arising from the African Continental Free Trade Area (AfCFTA), and Ethiopia’s current status in the process of accession to the World Trade Organization (WTO).
As business communities from various countries, including the Zhejiang Federation of Industry and Commerce of China, increasingly seek to work with our Chamber and gain a deeper understanding of Ethiopia’s trade and investment opportunities, it is essential that our Chamber strengthens its capacity to provide comprehensive, up-to-date, and analytical information tailored to the interests of different countries.
Furthermore, we should serve as a reliable and informative source by analyzing the benefits of national economic reforms, investment incentives and regulations in different sectors, as well as other relevant national, regional, continental, and global developments.
In addition, it is our responsibility to adequately assess the interests of foreign investors and facilitate their engagement with relevant sector ministries, commissions, and other institutions so that they can obtain the necessary support and information required to establish and expand their investments.
Beyond this, the Chamber should establish a system that enables effective monitoring of investment outcomes. This would allow us to evaluate how many investments have been fully or partially successful, identify challenges faced by unsuccessful projects, and analyze the underlying causes. Such findings should form the basis of discussion points in our joint public-private dialogue platforms (EPPDF) with government executive bodies.
Therefore, trade and investment promotion is not merely a globally accepted practice or one of the mandates entrusted to us by our establishment proclamation. It is also a critical means of creating opportunities for knowledge transfer, sharing business experience and best practices within the domestic private sector, generating employment, increasing foreign exchange earnings, and facilitating technology transfer.
Accordingly, my message is that all of us should actively operate within this strategic framework and contribute to advancing Ethiopia’s trade and investment promotion efforts.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

