Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 17, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ትግበራ ዙሪያ በሀዋሳ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ትግበራ ዙሪያ በሀዋሳ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
……………….
በምክር ቤቱ፣ GIZ AU እና በሲዳማ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ትብብር በተዘጋጀው ስልጠና በሲዳማ ክልልና በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ላኪዎች፣ አስመጪዎች፣ አምራቾች እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችን ተሳትፈዋል።

የስልጠናው ዋና ዓላማም የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የAfCFTA ስምምነት ፕሮቶኮሎችን፣ የንግድ ሂደቶችንና የአተገባበር መስፈርቶችን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ በማድረግ፣ በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማብቃት ነው።

የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስለ ስምምነቱ መሠረታዊ ሂደቶችና ሊሟሉ ስለሚገባቸው መስፈርቶች የተሻለ ግንዛቤ እንዳገኙና በቀጣይም በየሚሰማሩባቸው የንግድ ዘርፎች ላይ በትኩረት በመስራት በአፍሪካ ገበያ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል።
 
ኢትዮጵያ በAfCFTA ስምምነት በመጠቀም ምርቶችን ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመላክ አወንታዊ ውጤቶችን እያስመዘገበች ሲሆን፣ የአፍሪካን ሰፊ ገበያ በበለጠ ለመጠቀም የግሉን ዘርፍ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኢትዮጵያን የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለማድረግ ተከታታይ የግንዛቤ ማሳደጊያና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሠጠ ይገኛል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia