Oct 02, 2026 .
የንግድ ምክር ቤቶች የማሻሻያ አዋጅ በአፋጣኝ ሥራ ላይ እንዲውል የንግዱ ማኅበረሰብ ጠየቀ ::

የንግድ ምክር ቤቶች የማሻሻያ አዋጅ በአፋጣኝ ሥራ ላይ እንዲውል የንግዱ ማኅበረሰብ ጠየቀ ::
ሀገራዊ የኢኮኖሚ ለውጦችን ፍቱን በሆነ መልኩ ለመደገፍና የአባላትን ፍላጎት በብቃት ለማስተናገድ የሚያስችለው የንግድ ምክር ቤቶች ማሻሻያ አዋጅ በአፋጣኝ ሕግ ሆኖ እንዲወጣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት አሳስበዋል።
ማኅበረሰቡ እንደገለጸው፣ አሁን ላይ ሥራ ላይ ያሉት አሮጌ አዋጆች የዘመኑን የንግድ ሥርዓት ተለዋዋጭነት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት አዳጋች ሆነዋል።
በተለይ አዲሱ የዲጂታል ኢኮኖሚ፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማደግ እና የውድድር ከባቢያዊ ሁኔታዎች አዲስ አሰራርን የሚጠይቁ መሆናቸው ተመላክቷል።
አዋጁ መዘግየቱ የምክር ቤቶቹን የአገልግሎት አሰጣጥ አቅም እያቀጨጨው መሆኑን ባለድርሻ አካላት ይገልጻሉ። የንግድ ማኅበረሰቡ አክሎም፣ የተሻሻለው አዋጅ ሥራ ላይ መዋሉ የምክር ቤቶቹን ተጠያቂነትና ብቃት ከማሳደጉም በላይ፣ መንግሥት ከግሉ ዘርፍ ጋር የሚያደርገውን የፖሊሲ ውይይት እንደሚያቀላጥፈው ተናግረዋል።
አዋጁ ዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ የምክር ቤቶች የገቢ ምንጭ እንዲስፋፋ እና ለአባላት የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራት እንዲሻሻሉ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተመላክቷል። (ካፒታል)

