Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 05, 2026 .

ክቡር የትምጌታ አስራትን (ዶ/ር) የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በመሰየሙ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ- ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው መስራች ጉባኤ ክቡር የትምጌታ አስራትን (ዶ/ር) የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በመሰየሙ በመላው የግሉ ዘርፍ፣ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በራሴ ስም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በታታሪ የሰው ኃይል፣ በምርታማ መሬት፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እድሎች የታደለ ክልል ነው። ይህን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሥራ ዕድል፣ የምርታማነት እና የንግድ ማስፋፊያ ለመቀየር የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ቅንጅት ወሳኝ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ አዲስ አመራር ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት በመሥራት የኢንቨስትመንትና የንግድ አካባቢን የበለጠ እንደሚያሻሽል ተስፋ አደርጋለሁ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትም የግሉ ዘርፍን በማስተባበርና በመወከል ለክልሉ የኢኮኖሚ እና የንግድ ልማት አጋርነቱን ለማጠናከር ዝግጁ ነው።

በድጋሜ ለክቡር ዶ/ር የትምጌታ አስራት እና ለመላው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ሰላም፣ ስኬትና የተሻለ የልማት ጉዞ እመኛለሁ።

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia