የካይዘን የልህቀት ማዕከል እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት በይፋ አስጀመሩ።


የካይዘን የልህቀት ማዕከል እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በግሉ ዘርፍ የአሠራር ውጤታማነትን፣ ምርታማነትን እና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ያለመ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት በይፋ አስጀመሩ።
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ በስትራቴጂክ አጋርነቱ ማስጀመርያው ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የዚህ አጋርነቱ ያለውን ከፍተኛ አስፈላጊነት አብራርተዋል።

ዶክተር ዓይናለም በመልዕክታቸውም፤ ብክነትን በማስወገድ፣ አሠራርን በማሻሻል እና ቀጣይነት ባለው ዕድገት ላይ ያተኮረውን የካይዘን ፍልስፍና ለአገር ውስጥ ተቋማት ማስተዋወቅና መተግበር የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞችን ምርታማነትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተውበታል።

በዚህ የጋራ ትብብር አማካኝነት ሁለቱ ተቋማት ለአነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ለሚገኙ የንግድ ተቋማት የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችን፣ የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን እና የምክር አገልግሎቶችን ለመስጠት አቅደዋል።
ይህም ስምምነት በአገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሥራ ባህልን ለማዘመንና የመንግሥትና የግል ዘርፍ ውይይትን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልፀዋል።
የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) የኢትዮጵያ ቢሮ ከፍተኛ ተወካይ አቶ ካዙኪ ካያ በኩላቸዉ በመደበኛ ስምምነቶች እና በመግባቢያ ሰነዶች (MoU) በተቋማት የገቡ ቃል ኪዳኖች ኢንዱስትሪዎችና የንግድ ተቋማት ተጨባጭ እና ተግባራዊ ለውጦችን ማምጣት በሚችል መልኩ መተግበር እንዳለባቸዉ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
❇️❇️❇️❇️❇️❇️
Kaizen Excellence Center and ECCSA Launch Strategic Partnership to Drive Private Sector Productivity
The Kaizen Excellence Center (KEC) and the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) have officially launched a strategic partnership aimed at enhancing business efficiency, operational excellence, and overall competitiveness across Ethiopia’s private sector.
During the launch event, Dr. Aynalem Abayneh, Vice President of ECCSA, delivered the opening remarks, highlighting the critical importance of this collaboration. Dr. Aynalem emphasized that integrating the Kaizen philosophy focused on continuous improvement, waste reduction, and process optimization into local businesses is essential for elevating the productivity and global standards of Ethiopian enterprises.
Through this joint effort, KEC and ECCSA plan to deliver specialized training, capacity-building programs, and consultancy services tailored to support micro, small, and large scale businesses. The partnership marks a significant milestone in fostering public-private dialogue and modernizing workplace culture throughout the nation’s commercial and industrial sectors.
Mr. Kazuki Kaiya, Senior Representative of the JICA Ethiopia Office on his part , emphasized that formal agreements and Memorandum of Understanding (MoU) commitments must translate into tangible, real-world impacts for local industries and businesses.

