Oct 20, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የማኔጅመንት አባላት የም/ቤቱን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመርያዉን ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ገምግሟል።


የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የማኔጅመንት አባላት የም/ቤቱን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመርያዉን ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ገምግሟል።
በስራ አፈፃፀም ግምገማዉ ወቅት የም/ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የስራ አፈፃፀሙ ከአጠቃላይ የም/ቤቱ ዕቅድ አንፃር ሲታይ አበረታች ቢሆንም የየመሪያዎቹ በተናጠል ሲታይ ግን ትኩረት የሚሹ የስራ ክፍሎች መኖራቸዉን አፅንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።

የምክር ቤቱ የማኔጅመንት አባላት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዉ ሩብ አመት በታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ላይ በጥልቀት ከተወያዩ በኋላ በዋና ፀሐፊዉ የቀጣይ ሩብ አመት የትኩረት አቅጣጫዎች ተሰጥተዋል።

