የካፒታል ጋዜጣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ሰፊ፣ዝርዝርና ሙያዊ ቆይታ አድርጓል።

አሁን በስራ ላይ ያለው የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 341/95 የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶችን ሀገሪቱ እከተለዋለው ስትል ከነበረው የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አንፃር ከ24 ዓመታት በፊት ወደትግበራ የገባ አዋጅ ነው።
በአዋጁም በሀገሪቱ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ለማድረግ ምክር ቤቶች ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማስቻል እንዲሁም የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች የንግዱ ኅብረተሰብ አባላት ስለተሰማሩበት ሥራና በአጠቃላይ ስለአገሪቱ ኢኮኖሚ ልማት የሚወያዩበትና ለመንግሥት ሃሳብ የሚያቀርቡበት መድረክ ሆነው እንዲያገለግሉ በማስፈለጉ ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል።
ሆኖም ፤ አዋጁ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የገደበና ለአሰራር የማይመቹ አንቀፆችን የያዘ በመሆኑ እንዲሻሻል በተደጋጋሚ ሲጠየቅ ባጅቷል።
በተጨማሪም ፤ ሀገሪቱ አሁን እያደረገችው ባለው ስር ነቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንፃር ለግሉ ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ከፍ ያለ በመሆኑ አዋጁን ከነባራዊ ለውጦች ጋር ማጣጣም ተገቢ ስለመሆኑም ይነሳል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፤ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 341/95ን ለማሻሻል ያዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ያስፈለገበትን ምክንያቶች እና አሁን የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም በስራ ላይ ያለው አዋጅ ያሉበት ክፍቶች፣ እንዲሁም በተቋማት መካከል የተነሱ ከፍተኛ ትኩረት የሳቡ አለመግባባቶችን መፍታት ላይ የተደረጉ ጥረቶችን በተመለከተ
የካፒታል ጋዜጣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ሰፊ፣ዝርዝርና ሙያዊ ቆይታ አድርጓል።
ዶ/ር ቀነኒሳ በዚህ ቆይታቸው ከላይ ከተነሱ ጭብጦች ባሻገር ከአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ትስስር ጋር መራመድ የሚችል ዘመናዊ የንግድ ምክር ቤት ለመገንባት ያላቸውን ራዕይም ለጋዜጣው አጋርተዋል።
እኛም ለዛሬ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከጋዜጣው ጋር የነበራቸውን ቆይታ እናጋራችሁ። መልካም ንባብ
(ሊንኩን ከታች አያይዘናል)

