Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 17, 2026 .

በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ትግበራ ላይ ያተኮረ ስልጠና በሀዋሳ ሠጠ።

 

በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ትግበራ ላይ ያተኮረ ስልጠና በሀዋሳ ሠጠ።
………………………
ስልጠናው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት (ECCSA) ከGIZ AU እና ከሲዳማ ንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት (AfCFTA) ትግበራ ዙሪያ ያተኮረ ነው።

በሲዳማ ክልልና በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ላኪዎች፣ አስመጪዎች እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችን የስልጠናው ተሣታፊዎች ናቸው።

የኢትዮጵያ የንግድንል ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ ስልጠናው የኢትዮጵያ ነጋዴዎች በአፍሪካ ገበያ የበለጠ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የነጋዴው ማኅበረሰብ የAfCFTA ስምምነት ፕሮቶኮሎች፣ የንግድ ሂደቶችና የሥምምነቱን የመተግበሪያ ሂደቶች በአግባቡ እንዲረዳ ማድረግ የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ወይዘሮ ሔለን አብራርተዋል።

የሲዳማ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል ዶ/ር መላኩ አበራ በበኩላቸው፣ ስልጠናው የክልሉ ነጋዴዎች ስለAfCFTA በቂ ዕውቀት እንዲያገኙና በአፍሪካ ገበያ ውስጥ ተሳታፊ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

ስልጠናውን የሚሰጡት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ከሌሎች ተቋማት የተውጣጡ በዘርፉ ሰፊ ሙያዊ እውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ናቸው።

ነጋዴዎች የAfCFTA የንግድ ሥርዓትን፣ የንግድ ሂደቶችን፣ የጉምሩክ አሠራሮችን እና በሥምምነቱ የተፈጠሩ የአፍሪካ ገበያ ዕድሎችን በአግባቡ መረዳት እንዳለባቸው ይታመናል።

ኢትዮጵያ በቀጣናዊ የንግድ ሥምምነቱ አማካኝነት የንግድ ተሳትፎዋን በማስፋት ምርቶች ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተላኩ ሲሆን በተካሄዱ የንግድ ልውውጦችም አወንታዊ ውጤቶች መገኘታቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ አቅም ለማሣደግና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ቀጣይነት ያላቸውን ሥልጠናዎች እየሠጠ ነው።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia