Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 12, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በ“IFRS for SMEs” ዙሪያ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በ“IFRS for SMEs” ዙሪያ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡
ስልጠናው ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SMEs) በ“IFRS for SMEs” የሂሳብ አያያዝና የሪፖርት ሥርዓት ዙሪያ ለአራት ቀናት የሚሰጥ ነው፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ፣ ምክር ቤቱ ለአነስተኛና መካከለኛ ተቋማት ልዩ ትኩረት በመስጠት በታክስ፣ በሂሳብ አያያዝ፣ በአመራር፣ በአሠራር እንዲሁም የንግድ ሥራን ሊያሳልጡ በሚችሉ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

በምክር ቤቱ እና በP4G ትብብር በቢዝነስ አመራር አካዳሚ የሚሰጠው ይህ ሥልጠና፣ የኢንተርፕራይዞችን የሂሳብ አሠራርና የሪፖርት ሥርዓት የበለጠ ዘመናዊ፣ ተዓማኒና ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።

የ“IFRS for SMEs” ሥርዓት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተገቢና ቀላል የሆነ የሂሳብ አያያዝና የፋይናንስ ሪፖርት ሥርዓት በመዘርጋት የተቋማቱን የፋይናንስ መረጃ ጥራትና ተዓማኒነት ለማሻሻል የሚያግዝ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ አቅም ለመገንባት በተለያዩ የሥልጠና መስኮችና ብቃት ባላቸው አሠልጣኞች አማካኝነት ለተለያዩ ተቋማትና ለንግዱ ማኅበረሰብ ሥልጠናዎችን በመስጠት የግሉ ዘርፍ የአመራር፣ የአሠራርና የተወዳዳሪነት አቅም እንዲጎለብት እየሠራ ይገኛል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia