Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 07, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ለማ እና በዩኒቨርሲቲዉ የቢዝነስና  ኢኮኖሚክስ  ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ገዳ ጀበል ጋር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ለማ እና በዩኒቨርሲቲዉ የቢዝነስና  ኢኮኖሚክስ  ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ገዳ ጀበል ጋር በከፍተኛ ት/ርት ተቋማትና በግሉ ዘርፍ መካከል ሊኖር በሚገባ አጋርነት  ላይ ተወያይተዋል።
ዶ/ር ቀነኒሳ የም/ቤቱን ዓላማና ዋና ዋና ተልዕኮዎችን እንዲሁም  በቀጣይ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ለመሥራት የታቀዱ ተግባሮችን በማስመልከት ለዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ገለፃ አቅርበዋል።

ም/ቤቱ  የቢዝነስ ዲፕሎማሲን ከመደገፍ አንፃር ፣ ኢንቨስትመንትን ከማሳለጥ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማትን ከማጎልበት  እና የግሉን ዘርፍ የሰለጠነ የሰዉ ኃይል ፍላጎት መሠረት ያደረገ ስልጠና እንዲያገኙ ከማድረግ እና ሌሎች ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን ከማከናወን  አንፃር ከውጭ ጉዳይ፣ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር  እና ከሌሎች  የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት የልማት አጋሮች  ጋር እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።


የዉይይቱ ዋነኛ ዓላማም ዩኒቭርሲቲዎች የሚቀርጿቸዉና በስራ ላይ የሚያዉሏቸዉ  ካሪኩለሞች ለግሉ ዘርፍ ምርታማነትና  ዉጤታማነት ቀጥተኛ አስተዋፅኦ በሚያደርግ መልኩ መሆን በሚቻልበት  ሁኔታ ላይ ለመምከር ነዉ። ይህ እንዲሆን ደግሞ ዩኒቨርሲቲዎች የግሉ ዘርፍ ምን አይነት ክህሎትና ዕዉቀት ያላቸዉ የሰዉ ኃይል ይፈልጋል የሚለዉን በጥናት በመለየት በዚያ መሰረት ተመርቆ የሚወጣዉ የሰዉ ኃይል በገበያ ተፈላጊነት ያለዉ መሆኑን ማረጋገጥ  አለባቸዉ ብለዋል ዶ/ር ቀነኒሳ።

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ለማ በበኩላቸዉ የግሉን ዘርፍ ለማጠናከር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ብዙ መስራት እንደሚጠበቅባቸዉ ጠቅሰዉ እኛም በአከባቢያችን ካሉት ኢንዱስትሪዎች ጋር ያለንን አጋርነት በማጠናከር  የሚጠበቅብንን ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።

አጋርነታችንን ለማጠናከርም የግሉ ዘርፍ ወኪል ከሆነዉ የኢትዮጵያ  የንግድና ዘርፍ ማህቀራት ም/ቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም አለብንም ብለዋል።

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ገዳ ጀበል ከነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የግል ዘርፍ ተዋናዮች ጋር  የወጣቶች  ስራ ፈጠራን ለማጠናከር የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ጠቁመዉ ይህንን አጠናክረዉ ለመቀጠል ከከተማዉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ጋር ተቀናጅተን መስራት አለብን ብለዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia