የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማዕከላዊ ሪጅን የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማዕከላዊ ሪጅን የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማዕከላዊ ሪጅን የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር የሚያጠናክሩና ለሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትና ብልጽግና በሚያበረክቱ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በዲጂታላይዝሽን ዙሪያ ነው የተወያዩት።
አቶ ሰብስብ አባፊራ ሁለቱ ተቋማት በኢትዮጵያ ቀደምት ከሆኑ ሀገራዊ ተቋማት መካከል መሆናቸውን ገልጸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብና የፖሊሲ ባንክ መሆኑን፤ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ስኬት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ ያለ ተቋም መሆኑንና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትም የሀገሪቱ የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ማዕከል በመሆን ሚናቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት፣ ምቹ የንግድ አካባቢ ለመፍጠር፣ የወጪ ንግድን ለማሳደግ እና የኢትዮጵያ ምርቶችና አገልግሎቶች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ገበያ እንዲያገኙ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የግሉ ዘርፍ በቂ የፋይናንስና የብድር አገልግሎት እንዲያገኝ፣ በግብርና፣ በማምረቻ ኢንዱስትሪና በሌሎች ዘርፎች የፋይናንስ ተደራሽነት እንዲሻሻል እንዲሁም የኢትዮጵያን የ2030 የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ ስኬታማ ለማድረግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋነኛ አጋር እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማዕከላዊ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ ባንኩ ለንግዱ ማኅበረሰብ ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፣ Merchant App፣ Mobile Banking እና ሌሎች ዲጂታል አገልግሎቶች የንግድ ሥራዎችን ለማቀላጠፍ ሚናቸው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።
በተለይም በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ለንግዱ ማኅበረሰብ የተዘጋጀው CBE Connect የተሰኘው ዲጂታል አገልግሎት የባንኩን አገልግሎት በቀላሉናእንዲጠቀሙና ገንዘባቸውን በህጋዊ መንገድ እንዲላላኩ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
ሁለቱ ተቋማት የግሉን ዘርፍ የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ለማሳደግ፣ ዲጂታል የክፍያ ሥርዓቶችን ለማስፋፋት፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት፣ በስልጠናና አቅም ግንባታ እንዲሁም ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት በጋራ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት የበለጠ እንደሚያጠናክሩም ተጠቁሟል፡፡

