Feb 03, 2026 .
15ኛዉ ኢትዮ – ቻምበር አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ነገ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይከፈታል፡፡



15ኛዉ ኢትዮ – ቻምበር አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ነገ ይከፈታል፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢፌዴሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀዉ 15ኛዉ ኢትዮ-ቻምበር አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
የንግድ ትርኢቱ ረቡዕ፡ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአዲስ አበባ፡ መስቀል አደባባይ ይከፈታል፡፡


በመክፈቻ ፕሮግራሙም ሚኒስትሮችና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የአገራት አምባሳደሮች፣ የሀገር ውስጥ እና ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ኩባንያዎች ባለቤቶችና ሌሎች እንግዶች ይገኛሉ፡፡
በንግድ ትርኢቱ ከ300 በላይ የአገር ዉስጥ ድርጅቶችና ከ20 በላይ ከሚሆኑ የዉጭ አገራት የመጡ ከ50 በላይ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ።
ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየዉንና “የኢትዮጵያን ይግዙ! በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ!” በሚል የሚካሄደውን ይህን ታላቅ ዝግጅት ከ30 ሺ በላይ ህዝብ ይጎበኘዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይምጡ፣ እርስዎም ተጋብዘዋል!!

