Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com
Latest News
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባል ምክር ቤቶችን ተቋማዊ አቅም እንዲሁም የአሠራር ብቃትን ለማጠናከር የጀመረውን የአቅም ግንባታ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እያከናወነ ነው። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በተካሄደው 8ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ ተገለጸ። በንግድ ዘላቂነት እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት ስትራቴጂካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቋል። የካፒታል ጋዜጣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ሰፊ፣ዝርዝርና ሙያዊ ቆይታ አድርጓል። በተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራውና የምክር ቤቱን የቦርድ አባላት ያካተተው ልዑክ፣ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በኤግዚቢሽኑ ተሳትፏል። ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ማኅበረሰብ ጋር ማገናኘት የውጭ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉብኝቶቻችን ዋነኛ ዓላማ ነው።

Read more

Feb 05, 2026 .

15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት በመስቀል አደባባይ ተከፈተ።

15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት በመስቀል አደባባይ ተከፈተ።

በኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀው 15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት ከጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መስቀል አደባባይ መካሄድ ጀምሯል።

የንግድ ትርኢቱ ቁልፍ ዓላማዎች

ይህ ዓመታዊ መድረክ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን ያለመ ሲሆን፣ በዋናነት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ያተኩራል፦

* የሀገር ውስጥ ምርትን ማስተዋወቅ፦ የኢትዮጵያን ምርቶች፣ አገልግሎቶችና ጥሬ ዕቃዎች ለዓለም ገበያ ማሳየት።

* የቴክኖሎጂ ሽግግር፦ ለኢንዱስትሪ ልማትና ለሥራ ፈጠራ የሚያግዙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ።

* የገበያ ትስስር፦ በሀገር ውስጥና በውጭ ኩባንያዎች መካከል የ”አቻ ለአቻ” (B2B) የንግድ ውይይቶችን ማመቻቸት።
በዘንድሮው የንግድ ትርኢት ላይ የሚሳተፉት አካላት ስብጥር ሰፊ ሲሆን፦

* ከ20 በላይ ሀገራት የተውጣጡ፤
* ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች፤
* ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች
ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው ቀርበዋል።
የንንግድ ትርኢቱ ለሁሉም ጎብኚዎች ክፍትት ነዉዉዉ። ይዮጎብኙ፣የሚያሻዎትን ይሸምቱ።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia