የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድና የልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) ጋር ተወያየ፡፡


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድና የልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) ጋር ተወያየ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ንግድና የልማት ኮንፈረንስ የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲያኔ ሳይንዞጋ ጋር የግል ዘርፉን አቅም ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም እሴት የሚጨምሩ የኢትዮጵያ ወጪ ንግድን ከማበረታታት እና የገበያ ተደራሽነታቸውን ለማስፋት በግሉ ዘርፍ አቅም ግንባታ ላይ አብረው እንደሚሰሩ አፅንዖት ሰጥተው ተነጋግረውበታል፡፡
ምከር ቤቱ የኢትዮጵያን የግሉ ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማጎልበት ለአቅም ግንባታ ስራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዋና ፀሐፊው ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በተለይም ወቅቱ የሚጠይቃቸውን የዲጂታል ግብይት ክህሎታቸውን ለማሳደግ በምክር ቤቱ የቢዝነስ አመራር አካዳሚ በሰፊው ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድና የልማት ኮንፈረንስ የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲያኔ ሳይንዞጋ በበኩላቸው የአፍካ ንግድና ልማትን በመሳለጥ ላይ አትኩሮ የሚሰራው UNCTAD ዋና መስርያ ቤቱ በስዊዘርላንድ ጀኔቫ እንደሚገኝ ጠቁመው የአፍሪካ አህጉራዊ መስተባበርያ በአዲስ አበባ የተከፈተው በዋና መ/ቤት እና በአፍሪካ አህጉራዊ ማስተባበርያ ጽ/ቤቶች መካከል የአገናኝነት ሚናን ለመጫወት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ድርጅቱ እሴት ጨምረው ወደ ውጭ የሚልኩ ላኪዎችን ለማበረታታት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡


The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations held discussions with the United Nations Conference on Trade and Development (UNCTAD).
Dr. Kenenisa Lemi, Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, held fruitful discussions with Diane Sayinzoga, Head of the Africa Regional Office of the United Nations Conference on Trade and Development, at the United Nations Economic Commission for Africa on ways to strengthen the capacity of the private sector.
In their discussion, they emphasized that they will work together on capacity building in the private sector to promote value-added Ethiopian exports and expand their market access.
The Chamber is paying special attention to capacity building to enhance the competitiveness of the Ethiopian private sector, said Secretary General Dr. Kenenisa Lemi, explaining that extensive training is being provided at the Chamber’s Business Leadership Academy to enhance their digital marketing skills, which are in demand at the time.
Diane Sayinzoga, Head of the Regional Office for Africa at the United Nations Conference on Trade and Development, said that UNCTAD, which focuses on promoting trade and development in Africa, is headquartered in Geneva, Switzerland, and that the Regional Office for Africa is opened in Addis Ababa to play a liaison role between the headquarter and the regional Offices. She added that the organization will provide the necessary assistance to encourage exporters to add value and export.

