የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከመንግስት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከልማት አጋሮች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ንቁ የግል ዘርፍ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከመንግስት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከልማት አጋሮች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ንቁ የግል ዘርፍ እና ለንግድ ተስማሚ አካባቢን በመፍጠር ንግድ እና ኢንቨስትመንትን የማሳደግ፣ የአቅም ግንባታ ድጋፍ የመስጠት እና የምርምርና የአድቮኬሲ ሥራዎችን የማከናወን ኃላፊነት አለበት።
ሀገራዊ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቱ
የንግድ ማህበረሰቡን በንግድና ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ኩነቶችና ትእይንቶች ላይ ያሳትፋል፣የንግድ ትርኢቶች/ኤግዚቢሽን ያዘጋጃል፣
ሕግ ማማከር እና የግልግል ዳኝነት ይሰጣል
የንግድ ማውጫ ያዘጋጃል፣ ወቅታዊ የንግድ መረጃዎችን ለንግዱ ማህበረሰብ ይሰጣል፣
የአባላትን ተጨባጭ ተሞክሮዎች ያጋራል፣ድጋፍ ይሠጣል፣
ምክር ቤቱ የንግድ ግንኙነቶችን በመፍጠርና ያሉትንም በማጠናከር በዓለም አቀፍ የገበያ ስርዓት ውስጥ እውቅናን
እንዲያገኙ ያግዛል፣ ማህበራዊ ኃላፊነትን ያጠናክራል፣
የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ሥራዎች ይሠራል፣ መመሪያዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣
የአምራች አገር የምስክር ወረቀት ማረጋገጫ እንዲሁም የሰነድ ማረጋገጫ (የላኪዎች) አገልግሎት ይሠጣል፣
የንግድ ድጋፍ አገልግሎት ይሰጣል፣
ምክር ቤቱ የንግድ ሥራ ክህሎት በማሳደግ ከሌሎች የንግድ መሪዎች እና ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር እንዲገናኙ ዕድሎችን ያመቻቻል፤
የቴክኒክ እና የክህሎት ስልጠናዎችን ያመቻቻል፣በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ሥልጠና ይሠጣል፣ የንግድ ትምህርት ሴሚናሮችን ያዘጋጃል፣
የምርምር እና አድቮኬሲ ሥራዎች ይሠራል፣ የተለያዩ ህትመቶች ያወጣል፣

