የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤትና የካይዘን የልህቀት ማዕከል ስትራቴጅክ ትብብር ለኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ዘላቂ የአቅም ግንባታ ለማምጣት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የም/ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አስታወቁ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤትና የካይዘን የልህቀት ማዕከል ስትራቴጅክ ትብብር ለኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ዘላቂ የአቅም ግንባታ ለማምጣት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የም/ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አስታወቁ።
የትብብሩ ዋና ዓላማ የንግድ ድርጅቶችን ምርታማነት፣ ብቃት፣ የሥራ ጥራትና፤ የሀብትና የጊዜ ብክነት በመቀነስ እና ተወዳዳሪነትን በማሳደግ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ማሳደር መሆኑንም አስረድተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት የስትራቴጂክ ትብብሩ በይፋ መመስረትን ተከትሎ ለኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድና ለአባል ምክር ቤቶች ፕሬዚዳንቶችና ዋና ፀሐፊዎች ከካይዘን የልህቀት ማዕከልና ከጃፓን አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በካይዘን ፍልስፍና እና አመራር ላይ በቢሾፍቱ እየተሰጠ ባለዉ የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ነዉ።
የሁለቱ ተቋማት የስትራቴጂክ ትብብር ስኬት የሚለካው በሥልጠና ብዛት ሳይሆን በንግድ ድርጅቶችና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ በሚያመጣው ተጨባጭ ለውጥ ነዉ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ከሥልጠና ወደ ተግባር፣ ከዕውቀት ወደ ውጤት፣ ከጥቂት ተቋማት ወደ መላው የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ማስፋፋት የጋራ ትኩረታችን መሆን አለበትም ብለዋል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በቀጣይም የተቋማትን ትብብር በማጠናከር ዘላቂ ውጤት ለማምጣት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

